Skip to content Skip to footer

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለጥበቃ ሠራተኞች የወንጀል መከላከል ግንዛቤ ስልጠና ተሰጠ

📅 ሐምሌ 19፣ 2018 ዓ.ም

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለጥበቃ ሠራተኞች የወንጀል መከላከል ግንዛቤ ስልጠና ተሰጠ

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሚሰሩ የጥበቃ ሠራተኞች፣ ከኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጅማ በር ፖሊስ ጣቢያ ጋር በመተባበር “ወንጀልንእንዴት መከላከል እንችላለን?” በሚል ርዕስ የግንዛቤ ስልጠና ተሰጥቷል።

በስልጠናው የወንጀል መከላከል ላይ የጥበቃ ሠራተኞች ያላቸው ወሳኝ ሚና፣ አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን በንቃት መከታተል፣ በወቅቱ ለፖሊስ ማሳወቅ እና ከፖሊስ ጋር በቅንጅት መሥራት ለሆስፒታሉ ደህንነት ያለው ጠቀሜታ ተብራርቷል።

አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለታካሚዎች፣ ለሠራተኞችና ለጎብኚዎች ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ ለመፍጠር ከፀጥታ አካላት ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ ይቀጥላል።

የእርስዎ ጤና የእኛ ተልዕኮ ነው!!!

Follow us for more updates:

Follow ALERT Hospital

Stay connected for the latest updates.

Leave a Comment