የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የህብረተሰብ ጤና ለማስጠበቅ የጤና ግብዓት ስራዎች ላይ ባለፉት ዓመታት በሕግ፣ በአደረጃጀትና በአሠራር ባደረጋቸው ተከታታይ ማሻሻያዎች በ64 የተለያዩ መለኪያዎች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘት ችሏል። ይህ እውቅና ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ በሰራቻቸው ጠንካራ የቁጥጥር ሥርዓቶች እና የማሻሻያ ስራዎች የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የመድኃኒት ቁጥጥር ስርዓት ብስለት ደረጃ (Maturity Level) ላይ መድረሷን አረጋግጧል።
የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ክፍል ከባለስልጣን መስሪያቤቱ ጋር ያላቸውን የሥራ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር፣ ለህዝቡ የሚቀርቡ የመድኃኒት ምርቶች ጥራት፣ ደህንነት እና ፈዋሽነት ተረጋግጦ እንዲቀርብ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ውጤታማ ጉብኝቶች ተደርገዋል።
አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታካሚ ተኮር፣ ከፍተኛ ጥራት ያለውና ርህራሄን መሰረት ያደረገ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ ነው።
“የእርስዎ ጤና የእኛ ተልዕኮ ነው!”
