Skip to content Skip to footer

የአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የክረምት በጎ አድራጎት ቴክኒካል ቡድን የነፃ የህክምና ዘመቻውን ተደራሽነትና ውጤታማነት የበለጠ ለማጠናከር የዝግጅትና የማስተባበሪያ ውይይት አካሄደ

📍ዛሬ | ሐምሌ 15፣ 2018 ዓ.ም

የአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የክረምት በጎ አድራጎት ቴክኒካል ቡድን የነፃ የህክምና ዘመቻውን ተደራሽነትና ውጤታማነት የበለጠ ለማጠናከር የዝግጅትና የማስተባበሪያ ውይይት አካሄደ።

በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሃ ግብር ዋና ዋና እቅዶች፦

🔹 ለ120,000 ዜጎች ነፃ የጤና ምርመራና ህክምና አገልግሎት መስጠት

🔹 20,000 ችግኞችን መትከል፣ ለመድኃኒት ምርምር የሚውሉ ችግኞችን ጨምሮ

🔹 ለ200 ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን ማቅረብ

🔹 ህፃናትንና ወጣቶችን በማሳተፍ የማነቃቂያና የግንዛቤ መድረኮችን ማዘጋጀት

🔹 ለታካሚዎች፣ ለታካሚ ቤተሰቦችና ለዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች የማዕድ ማጋራት

🔹 የደም ልገሳ መርሃ ግብሮችን ማካሄድ

🔹 መዋዕለ ህፃናት መገንባት፣ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ማደስ እና የአካባቢ ፅዳት ዘመቻዎችን ማካሄድ

🔹 ለቀዶ ህክምና ወረፋ የሚጠብቁ ታካሚዎችን በልዩ ትኩረት በመለየት፣ ሀይልና ግብዓትን በማጠናከር በዘመቻ መልክ አገልግሎቱን ማዳረስ

🔹 የሌማት ቱሩፋት ሥራዎችን ማጠናከር

“የእርስዎ ጤና የእኛ ተልዕኮ ነው!”

Follow ALERT Hospital

Stay connected for the latest updates.

Leave a Comment