Skip to content Skip to footer

የሐኪሞችን ቀን በአብሮነትና በቡድን ስራ ማክበር

📍 ሐምሌ 30፣ 2018 ዓ.ም

የሐኪሞችን ቀን በአብሮነትና በቡድን ስራ ማክበር

አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “ሐምሌን ለሐኪሞች!” በሚል መሪ ቃል ዘጠነኛውን ሀገራዊ የሐኪሞች ቀን በተለያዩ የበጎ ተግባር፣ የደም ልገሳ፣ የስፖርትና የፓናል ውይይት መርሃ-ግብሮች አክብሯል።

የማጠቃለያ መርሃ-ግብሩም በኢትዮጵያ የሐኪሞች ማህበር (EMA) ተሳትፎ፣ የቡድን ስራን፣ አብሮነትንና ለሕዝብ ጤና የሚደረገውን ቁርጠኝነት በማጠናከር ተካሂዷል።

ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሐኪሞች፣ በምርምርና በተገልጋይ እርካታ ላበረከቱ የሥራ ክፍሎች እና ለፕሮግራሙ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አጋር አካላት እውቅናና ሽልማት ተበርክቷል። 🏆

“የእርስዎ ጤና፣ የእኛ ተልዕኮ ነው!”
Follow us for more updates

Follow ALERT Hospital

Stay connected for the latest updates.

Leave a Comment