
አለርት (ALERT) ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ለኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የቀድሞ አገልጋዮች እና ለመላው የኢንስቲትዩቱ ቤተሰቦች ለ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓላችሁ ከልብ የመነጨ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፋል!
🔬 የ100 ዓመታት የላቀ አሻራ፦
✍️ በህብረተሰብ ጤና ምርምር እና የላቦራቶሪ አገልግሎት፣
✍️ በበሽታዎች ቅድመ መከላከል እና ወረርሽኝ ቁጥጥር፣
✍️ በሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ በተመሠረተ የጤና ፖሊሲ ድጋፍ፣
✍️ የጤና ተቋማትን በመደገፍና በማብቃት፤
በተለያዩ የህዝብ ጤና ፈተናዎች ወቅት ያሳያችሁት የላቀ ሙያዊ ብቃት፣ ቁርጠኝነት እና ትጋት ለሀገራችን የጤና ዘርፍ ታላቅ ኩራት ነው። ከአለርት ሆስፒታል ጋር ያለው የረጅም ጊዜ የሙያ ትብብር በቀጣይም በምርምር፣ በስልጠና እና በህብረተሰብ ጤና አገልግሎት ላይ ይበልጥ ፍሬያማ እንዲሆን በጋራ የበለጠ እንሰራለን።
መልካም 100ኛ ዓመት! ✨🎉
#EPHI100 #ALERTHospital #PublicHealth #Ethiopia #HealthResearch #CentennialAnniversary