Skip to content Skip to footer

የቀድሞ ባለሙያዎች የአለርት ሆስፒታልን የለውጥ ጉዞ ጎበኙ!

📅 መስከረም 8/2019 ዓ.ም

በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በኤክስሬ፣ ፊዚዮቴራፒ፣ ፋርማሲ እና አስተዳደር ክፍሎች በተለያዩ ጊዜያት ሲያገለግሉ የነበሩ የቀድሞ ባለሙያዎች ሆስፒታሉን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም የሆስፒታሉን የተለያዩ ክፍሎችና ግቢ በመጎብኘት፣ በቅርብ ዓመታት የተመዘገበውን ለውጥና እድገት በመመልከት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ሆስፒታሉን ከዚህ በበለጠ ደረጃ ላይ ማየት እንፈልጋለን” ያሉት የቀድሞ ባለሙያዎቹ፣ በሆስፒታሉ ግቢ የተጀመሩ የግንባታና የልማት ሥራዎች በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀው ለታካሚዎች የተሻለ አገልግሎት እንዲውሉ መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የአለርት ታሪክ በትውስታ ይኖራል፤ ለውጡ ዛሬ ይቀጥላል፤ ተስፋው ነገን ይገነባል።

ያለፈው ትውስታ • የዛሬው ለውጥ • የነገው ተስፋ!

🩺 “የእርሶ ጤና የኛ ተልዕኮ!”

Follow us for more updates:

Follow ALERT Hospital

Stay connected for the latest updates.

Leave a Comment