
የዶ/ር ፀጋዬ ገ/አናንያን ሕልፈተ ሕይወት ተከትሎ፣ ዛሬ ነሐሴ 15፣ 2018 ዓም የአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና የአቤት ሆስፒታል ሠራተኞች፣ ቤተሰቦች፣ ወዳጆችና የቅርብ ጓደኞቺ በተገኙበት ለእርሳቸው መታሰቢያ የፀሎትና የሻማ ማብራት መርሃ ግብር ተከናውኗል።
በመርሃ ግብሩም ዶ/ር ፀጋዬ በሙያቸው፣ በሰው አክባሪነታቸውና በማህበረሰብ አገልግሎታቸው ያበረከቱት የማይረሳ አስተዋጽኦ በመዘከር፣ ለነፍሳቸው ዕረፍት እና ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጆቻቸው መጽናናት ፀሎት ተደርጓል።
ፈጣሪ ነፍሳቸውን በሰላም ያሳርፍ፤ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው የጤና ሙያ ማኅበረሰብ ጽናትና መጽናናትን ይስጥ።
Alert Comprehensive Specialized Hospital
Follow us for more updates