
በአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ሲያገለግሉ የነበሩትና እስከ ሕይወታቸው ማለፊያ ድረስ የአቤት ሆስፒታል ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ጸጋዬ ገብረ አናንያ በገጠማቸው ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት በሞት ስለተለዩን፣ የሆስፒታሉ አመራሮችና ሠራተኞች የተሰማንን እጅግ ከፍተኛ ሀዘን እንገልጻለን።
ዶ/ር ጸጋዬ ሕሙማንን በማገልገል፣ የጤና አገልግሎትን ጥራት በማሻሻል እና በሕክምናው ዘርፍ ጠንካራ አመራር በመስጠት ሙያዊ ሕይወታቸውን ያሳለፉ ታላቅ ባለሙያ ነበሩ።
አመራራቸው፣ ሙያዊ ብቃታቸው እና ለሕክምና የነበራቸው ቁርጠኝነት በከፍተኛ ክብርና ምስጋና ይታወሳል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው፣ ለባልደረቦቻቸው እና እርሳቸውን ለሚያውቁና አብረዋቸው ለሠሩ ሁሉ ከልብ የመነጨ ሀዘናችንን እንገልጻለን።
አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል